የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎት እንዲጣጣም ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት እንደሚገባቸው ተገለጸ::
የሲሚንቶ አምራቾች ማህበርና የሲሚንቶ አምራቾች ባለቤቶች ማህበር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም÷በተለያዩ የፀጥታ ችግሮችና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ምርት ያቆሙና በሙሉ አቅማቸው የማያመርቱ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ገልጸዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታም መፋጠን እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
ምርት አቁሞ የነበረው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል::
ፋብሪካው በቅርቡ ስራ እንዲጀምር ለማድረግም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንደሚላኩ ተመላክቷል፡፡
የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት ማቆሙ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እንዲቀንስ አድርጎት እንደነበረም ነው የተገለጸው ።
ቸርቻሪዎችም የሚሸጡበትን የሲሚንቶ ዋጋ የመለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው::
በዘቢብ ተክላይና መሳፍንት እያዩ