የጤና ባለሙያዎች ስለኮሮና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የመዲናዋ ጎዳናዎች በመዘዋወር ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጡ።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱን የሰጡት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ህሙማንና ህፃናት መርጃ ማዕከል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ሐኪሞችና ነርሶችን ያካተተው ቡድን በሙያቸው ህሙማኑን ለመንከባከብ እየሰሩ በመሆኑ÷ ነዋሪዎች በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ እንዲደርጉ መጠየቃቸው ነው የተገለጸው፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ እጅን መታጠብ፣ በእጅ አለጨባበጥ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን መግታትየሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸው ተገልጿል፡፡
ምልክቶች ከተስተዋሉ ሌሎችን ላለመጉዳት መጠንቀቅና ወደ ህክምና መሄድ የሚሉት መልዕክቶችም መካተታቸው ነው የተነገረው፡፡
ከዚያም ባለፈ ባለሙያዎች ወረርሽኙ ተገቢውን እንክብካቤና እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡