በኦሮሚያ በመተግበር ላይ ያለው የቡና ልማት ተነሳሽነት ዘርፉን ከፍ ወዳለ ምዕራፍ እያሻገረው ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመተግበር ላይ ያለው የቡና ልማት ተነሳሽነት ዘርፉን ከፍ ወዳለ ምዕራፍ እያሻገረው መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።
አቶ ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል ባወጡት መረጃ፥ 2011 ዓመተ ምህረት ላይ የክልሉ መንግስት የቡና ልማት ዘርፍን ወደፊት ለማራመድ ነቀምቴ ላይ አዲስ ተነሳሽነት ይፋ አድርጎ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውሰዋል።
ይህንንም ተከትሎ በክልሉ በቡና ተክል የተሸፈነ መሬት ስፋት አሁን ላይ በእጥፍ ማደጉን ገልፀዋል።
ምርታማነትም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ የሀገሪቱን የቡና የወጪ ንግድን ማሳደጉን ነው ያመለከቱት።
ይህም ሁኔታ አርሶ አደሩ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል አቶ ሽመልስ።