Fana: At a Speed of Life!

ፀሃይ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ማሳደጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፀሃይ ባንክ ስራ በጀመረ በአራት ወራት ውስጥ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ማሳደጉን ገልጿል።

ፀሃይ ባንክ አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ብርቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቀጠል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ባንኩ የባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡

የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 2 ቢሊየን 867 ሚሊየን 466 ሺህ ብር ከነበረበት 2 ቢሊየን 162 ሚሊየን 564 ሺህ ብር በመጨመር ካፒታሉ ወደ 5 ቢሊየን ብር አሳድጓል።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታዬ ዲበኩሉ እንደገለጹት÷ባንኩ አገልግሎት የሚሰጡ ከ45 በላይ ቅርንጫፎች አሉት፡፡

እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ወደ 100 ቅርንጫፎች ለማድረስ እንዲሁም የደንበኞቹን ቁጥር 356 ሺህ ለማድረስ ባንኩ እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

 

በቅድስት ብርሃኑ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.