ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከግብር በፊት 1 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር ማትረፉን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው 2021/22 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር ማትረፉን ገለጸ፡፡
ባንኩ ባካሄደው የባለአክሲዮኖች 23ኛ መደበኛና 19ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ÷ ተከታታይነት ያለው ስኬት ማስመዝገቡን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
በዚህም በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ የተከሰቱ የኢኮኖሚና ንግድ እንቅስቃሴ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በተጠናቀቀው 2021/22 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር ማትረፉ ተገልጿል፡፡
ይህም ከቀደመው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ139 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተጠቆመው፡፡
የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠንም 49 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር የደረሰ ሲሆን÷ ከባለፈው ዓመት የ14 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ሃብትም 61 ነጥብ 49 ቢሊየን ብር ካፒታል ማስመዝገቡንና ካለፈው ዓመት 7 ነጥብ 3 ቢሊየን ወይም በ 13 ነጥብ 45 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
በትዕግስት አስማማው