የብልፅግና ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሀገር አቀፉን የሴቶች የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር አስጀመሩ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ሚሊየን ሴቶች የሚሳተፉበት የሴቶች የሌማት ትሩፋትን በቢሾፍቱ ከተማ አስጀመሩ።
መርሐ ግብሩ “የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ ሁሉንም ከደጄ አመርታለሁ” በሚል መሪ ቃል ጋር መጀመሩን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አስታውቀዋል።
በመርሐ ግብሩ በከተማ ግብርና፣ በእንስሳት እርባታና በተለያዩ የስራ ዘርፎች ውጤታማ ስራ ያስመዘገቡ ሴቶችን የስራ ቦታ በመጎብኘት የዘር ርክክብ መደረጉንም ጠቅሰዋል።
“ዋናው ጉዳይ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ድህነትን እና ኋላ ቀርነትን የሚቋቋም ኢኮኖሚ በመገንባት እና ሌማትን ከራስ አልፎ በመላክ ለጎረቤት ሀገራት ማጋራት መሆኑንም ነው ያስተወቁት።
ሙሉ ትኩረቱ ግን ግን የህዝቡን ህይወት በተጨባጭ የሚቀይር ስራ መሥራት መሆኑንም ገልጸዋል።