ኮሮናቫይረስን ለመከላከል መመርያዎችን መተግበር ላይ ገና ብዙ ይቀረናል-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚተላለፉ መመርያዎችን በመተግበር ገና ብዙ እንደሚቀር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለፁ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ዙሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ የታዘቡትን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንቷ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፥ “ዛሬ በአዲስ አበባ ተዘዋውሬ ነበር፤ መመርያዎችን በመተግበር ገና ብዙ ይቀረናል” ብለዋል።
“የሚጠጋን ቫይረስ የለም ሲሉ የነበሩ ያሉበትን እያየን አንዘናጋ፤ ምርመራ በብዛት ባለመደረጉ ትክለኛውን ሁኔታ አላየንምና በሀገር ደረጃ ተቀንጅተን መዘጋጀት አለብን” ሲሉም ሲሉም ገልፀዋል።
ኮሮናቫይረስ እንዳይስፋፋ ለማድረግና ለመከላከል መንግሥት ተጨማሪ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ የሕዝብን ጤንነትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚደረግ ሁሉ በዛ ሊባል አይችልም ብለዋል።
“ቫይረሱን ለመከላከል የሚወጡ መመሪያዎችን መተግበር የእኛም ፋንታ ነው፤ የጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ አንዘናጋ፣ በጣሙን አደራ” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።