Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የተለየ ውሳኔ እስከሚጣቸው ድረስ ስራቸውን ቤት ውስጥ ሆነው እንዲያከናውኑ ውሳኔ አሳለፈ።

የክልሉ የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው ጉዳዩን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች፣ የጡረታ መውጫ ጊዜያቸው የደረሱ ሰራተኞች፣ የቆየ እና በሀኪም ማስረጃ የተደገፈ የጤና እክል ያለባቸው ሰራተኞች ከዚህ የተለየ ተለዋጭ ማብራሪያ እስከሚመጣ ድረስ በቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲከውኑ የክልሉ መንግስት መወሰኑን ገልፀዋል።

የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የመብራት ኃይል፣ ውሃ እና ትራንስፖርት ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ከቀደመው ስራቸው በላቀ በቁርጠኝነት በሙሉ አቅማቸው ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ የክልሉ መንግስት ጠይቋል ብለዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.