የተመድ ዋና ጸሃፊ ጉተሬዝ የተደረሰውን ስምምነት አደነቁ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደነቁ፡፡
ዋና ጸሃፊው ስምምነቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ፥ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙን በደስታ እንቀበለዋለን ብለዋል።
ስምምነቱ ለሁለት ዓመታት ያስቆጠረውን ግጭት ለማስቆም ወሳኝ የመጀመሪያ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ዋና ጸሃፊው ስምምነቱን መላው ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲደግፈው ጠይቀዋል፡፡
ጉቴሬዝ በሁለቱም ወገኖች ለተደረሰው ስምምነት ተፈፃሚነት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!