Fana: At a Speed of Life!

በሩብ ዓመቱ ከወጪ ንግድ 959 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከወጪ ንግድ 959 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሩብ ዓመቱ ከወጪ ንግድ 1 ቢሊየን 120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የእቅዱን 85 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት መቻሉንም ነው የገለጸው።
ከዚህ ውስጥ ግብርና 81 ነጥብ 03 በመቶ፣ የማምረቻው ዘርፍ 9 ነጥብ 63 በመቶ፣ ማዕድን 6 ነጥብ 1 በመቶ እንዲሁም አሌክትሪክ እና ሌሎች ምርቶች 3 ነጥብ 24 በመቶ ድርሻ አስመዝግበዋል፡፡
በቀጣይ ምርቶችን በክምችት የመያዝ አዝማሚያዎችን በመግታት፣ የህገ ወጥና ኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥሩን በማጠናከር፣ የድንበር ላይ ንግድ አፈፃፀሙን ከህጋዊ አሠራሩ ጋር የማስተሳሰርና የገበያ መዳረሻዎችን በማስፋት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.