Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የ4ኛ ሣምንት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የ4ኛ ሣምንት መርሐ ግብር በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው፡፡

የ4ኛ ሣምንት የሳይበር ደህንነት ወር መርሐ ግብሩ የማህበረሰብ አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የዜጎችንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማሳደግና ባህል በመገንባት ረገድ ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች የሚሰራበት ሳምንት ነው፡፡

ውይይቱ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የሀገርን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥና ዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ የሚሰሩ ሥራዎችን፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ የሰው ሃይል ልማት እንዲሁም የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ላይ የተሰሩ ሥራዎችን በጉልህ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በቀጣይም ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ በኩል ሊሰሩ የሚገቡ ሥራዎች ላይ ምክክሩ ቀጥሏል፡፡

በመርሐ ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት፥ የሕግ አውጪው፣ የሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው አካል በሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ዙሪያ የሚወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ፡፡

በተጨማሪ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚከታተሏቸውና የሚቆጣጠሯቸው ተቋማትም የሳይበር ደህንነት ጉዳይን ስትራቴጂክ ተቋማዊ ጉዳያቸው አድርገው እንዲመሩ ማስገንዘብ ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.