በብራዚል ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሉላ ዳ ሲልቫ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ሀገሪቱን የመሩት ሉላ ዳ ሲልቫ በስልጣን ላይ የነበሩትን ዣዬ ቦልሶናሮን አሸነፉ።
በመጨረሻው የድምፅ አሰጣጥ ሉላ ዳ ሲልቫ 50 ነጥብ 9 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።
በፈረንጆቹ 2018 ላይ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሉላ ዳ ሲልቫ በሙስና ወንጀል ተከሰው እስር ላይ የነበሩ በመሆናቸው ሳይወዳደሩ ቀርተዋል።
የዘንድሮው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የተደረገበት እና ውጥረት የነገሰበት ቅስቀሳዎችን ያስተናገደ ነው።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በዜጎች መካከል የታየው መከፋፈል ቶሎ እንደማይጠፋም ይገመታል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ እና አልጀዚራ