Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል የባህል መድሃኒቶች በጤና ስትራቴጂዋ ትኩረት እንደሰጠች የጤና ሚኒስትሯ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህላዊ ሕክምና በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለዘመናዊ ሕክምና መሰረት ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በየም ልዩ ወረዳ በቦር ተራራ ዓመታዊ የባህል መድሐኒት ለቀማ ተካሂዷል፡፡

ዶክታር ሊያ በዚሁ ወቅት፥ 80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ባህላዊ መድሐኒት እንደሚጠቀም ጥናቶች እንደሚያመላክቱ ነው የገለፁት፡፡

የጤና ሚኒስቴርም በስትራቴጂክ ዕቅዱ ለሀገር በቀል የባህል መድሃኒቶች እና እውቀቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡

የየም ብሔረሰብ ተነግሮ የማያልቅ ታሪክ አለው ያሉት ደግሞ  የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርዕቱ ይርዳ ናቸው፡፡

የብሔረሰቡ ባህላዊ የመድሐኒት ለቀማ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው በተጨማሪ የቱሪስት መስህብ ስፍራ ሊሆን የሚችል ቱባ ባህል በመሆኑ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰርበታልም ነው ያሉት፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ራሱን የቻለ አደረጃጀት በማቋቋም ሀገራዊ እሴቶችንና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን የሚያጠና፣ የሚያስተዋውቅ ዘርፍ አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የየም ብሔረሰብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅምት 17 ቀን በቦር ተራራ ለአንስሳትና ለሰው መድሐኒት ይለቅማል፣ ይህም በብሔረሰቡ ሳሞኤታ ተብሎ ይጠራል፡፡

በተመስገን  አለባቸው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.