የኢትዮጵያን ቡና ጥራት ማሳደግ የሚያስችል የ2 ሚሊየን ዩሮ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ቡና ጥራት እና ዋጋ ማሳደግ የሚያስችል የሁለት ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር ነው የተፈራረመው፡፡
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በቡናው ዘርፍ የሚከናወኑ ኢንቨስትመንቶች ያለባቸውን የአደጋ ተጋላጭነት መቀነስ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህም የኢትዮጵያን ቡና ብዛት፣ ጥራት እና ተፈላጊነት ማሳደግ የሚያስችል እንደሆነ መገለጹን በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡