Fana: At a Speed of Life!

በየካ ክ/ከተማ ከ182 ሺህ 400 ብር በላይ ሐሰተኛ ገንዘብ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ልዩ ስሙ 02 አካባቢ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ182 ሺህ 400 ብር በላይ ሐሰተኛ ገንዘብ ተያዘ፡፡

ከተያዘው ሐሰተኛ ገንዘብ ውስጥም ባለ 200 የብር ኖት 150 ሺህ 400 ብር፣ ባለ 100 የብር ኖት ደግሞ 32 ሺህ ብር እንደሚገኝበት ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ለጊዜውያልተለዩ ባለ 200 የብር ኖት 38 ሺህ 400 ብር እና ባለ100 የብር ኖት 28 ሺህ 800 ብር መያዙን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በአጠቃላይ 249 ሺህ 600 ብር ፣ 2 ፕሪንተር ማሽን እና ሌሎች ቁሳቁስ ከተጠርጣው ጋር በፌደራል ፖሊስ መያዙን የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.