የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 25 ኢትዮጵያውያን በማላዊ “ሞተው ተገኝተዋል” በሚል የተሰራጨውን ዘገባ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 25 ኢትዮጵያውያን በማላዊ “ሞተው ተገኝተዋል” በሚል የተሰራጨውን ዘገባ ከማላዊ መንግሥት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምዚምባ በሚባለው የማላዊ ሰሜናዊ ግዛት በሚገኝ ጥብቅ ደን ውስጥ በተገኘ የጅምላ መቃብር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስክሬን እንደተገኘ የሀገሪቱን ፖሊስ ዋቢ አድርገው የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ባውጣው መግለጫም÷25 ኢትዮጵያውያን በማላዊ “ሞተው ተገኝተዋል” በሚል የተሰራጨውን ዘገባ ከማላዊ መንግሥት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!