Fana: At a Speed of Life!

በደማችን ያስከበርናበደማችን ያስከበርናትን ሰንደቅ ዓላማ በላባችን ከፍ እናደርጋታለን-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትትን ሰንደቅ ዓላማ በላባችን ከፍ እናደርጋታለን!

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደማችን ያስከበርናትን ሰንደቅ ዓላማ በላባችን ከፍ እናደርጋታለን ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

ኮሙኒኬሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ 15ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ እንደሚል ገልጿል፡፡

ቀኑን ስናከብር በደም ጠብቀን ያቆያናትን ሀገራችንን በደማችን እና በላባችን እያጸናን ነው፤ ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ምልክት ነው ብሏል መግለጫው።

ይህንን ዓርማ ይዘው ጀግኖች መሥዋዕትነት ከፍለዋል፤በዓለም አደባባይአሸንፈዋል፤ይህ ሰንደቅ ዓላም ከልጅ እስከ ዐዋቂ ልብ ውስጥ የማይፋቅ ማኅተም አሳርፏል።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የትናንት የጋራ ታሪካችንን፤ የዛሬ ጥረታችንን እና የነገ ተስፋችንን እንዲሁምኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችን እና የማንነታችን ማኅተምነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ሰንደቅ ዓላማዋን አንግበው ለሉዓላዊነቷ እና ለአንድነቷ የተዋደቁየጀግኖች ልጆች እናት ናት ያለው መግለጫው አሁን ባለንበት ዘመንም ቢሆን ሰንደቅዓላማዋን አንግቦ፣ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የተነሡ ጠላቶቿን አሳፍሮ የሚመልስ ትውልድ ያላት፣ የእልፍ ጥቁር አንበሶች ምድር መሆኗንም ገልጿል፡፡

የቅርብ እና የሩቅ ጠላቶቻችን ከሀገር ውስጥ ባንዳ አሸባሪዎች ጋርተባብረው ኢትዮጵያን ለመበታተን መሄድ እስከሚችሉት ድረስ ተጉዘዋል፤ሆኖም በልጆቿ ደምና ብርታት ምኞታቸዉ ቅዠት ሆኖ ቀርቷል ነው ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ፡፡

እኛ ካልመራናት ትፍረስ ብለው፣ በየአካባቢው ግጭት ጠንሰሰው፣ ጠብን ስፖንሰር አድረገው ሕዝባችንን ተስፋ ለማስቆረጥ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡

እያንዳንዱ የሀገር ብተና ሤራቸው ተራ በተራ ሲከሽፍባቸው ደግሞ ሀገር ጠባቂ መከላከያ ሠራዊታችንን በሌሊት አጥቅተው ጦርነት ከፍተውብናል፤ይህ ሁሉ ወጥመድ ግን ለሰንደቃቸውክብር በሚሠዉጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች የጋራ ርብርብ ከግቡ ሳይደርስ መክኖ ቀርቷል ነው ያለው መግለጫው፡፡

በተለይም የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች በሀገራችን ላይ ጦርነት የከፈቱ አሸባሪዎችን ድል ነሥተው፤ ሀገራቸውን ከመፍረስ ታድገዋል፤በደማቸው ሰንደቅ ዓላማችንን አስከብረዋል፡፡

ጠላቶቻችን ጦርነት የከፈቱብን ሁሉንም ትኩረታችንን ወደ ጦር ግንባር አድርገን በሌሎች ዘርፎች ሽባ እንድንሆን አስበው ነበር፤ ዓላማቸው ኢትዮጵያን አዳክሞ ማፍረስ ነበር፤ነገር ግን ይህ ዓላማቸው በቁርጥ ቀን ልጆቿ ብርታትና እና በሕዝባችን ድጋፍ ሳይሳካ ቀርቷል ተብሏል በመግለጫው፡፡

“በደማችን እየጠበቅን በላባችን እናጸናለን” በሚል ዕሳቤ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከ ጫፍ በአንድ እጃቸው እያረሱ፤ በሌላኛው እጃቸው እየተኮሱ ሀገራቸውን እየገነቡ ነው ያለው መግለጫው በአንድ በኩል ከጠላት እየተከላከሉ፣ በሌላ በኩል የሰብል ምርታቸውን በብዙ እጥፍ ማሳደጋቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ሂደትም ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የግብርና ምርቶችን በማምረት፤ እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ የተጀመሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ወደላቀ ምዕራፍ በማድረስ እና ሌሎቹንም በማጠናቀቅ ሕዝቦችን ተስፋ ሊያስቆርጡ የተነሡ ጠላቶቿን ተስፋ ማስቆረጧን መግለጫው አንስቷን፡፡

በዚህም የሀገር ክብርና ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ እንዲል ተደርጓል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የልማት ሥራዎችን እያጧጧፉ ጎን ለጎን የተከፈተባቸውን ጦርነት ሲመክቱ፤ ዐዋቂ እና ወጣት አትሌቶቻችን ደግሞ በዓለም አደባባይ በሀገር ፍቅር ስሜት ተናበው የሀገራቸውን አሸናፊነት ለወዳጅም ለጠላትም ማወጃቸውንም መግለጫው አስታውሷል፡፡

ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገው አውለብልበዋል፤ከሀገር አልፈው የአፍሪካ ኩራት ሆነዋል፡፡

ኢትዮጵያችን በብዙ ፈተና በተወጠረችበት በዚህ ወቅት ጠላቶቿን እየመከተች የልማት ሥራዎችን በታላቅ ስኬት ቀጥላበታለች ፤የምግብ ሉዓላዊነት ሳይኖር የሀገር ሉዓላዊነትን ማስከበር ከባድ መሆኑ ተገልጿል።

በልመና ስንዴ የሰንደቅ ዓላማ ክብርን በዘላቂነት ማረጋገጥ አዳጋች ነው ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ጀግኖቻችን በጦር ግንባር በደም ያስከበሯትን ሰንደቅ ዓላማ፤ በልማት ትግል በላባችን ከፍ ለማድረግ፣ ሁሉም በተሠማራበት መስክ የበኩሉን መወጣት ይኖርበታል ሲልም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.