ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2015፣ ( ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህር ዳር ሲደርሱም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን፥ ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ ለመካፈል የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።
በአልዓዛር ታደለ