Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን የ4 አመት ህፃን ልጅ በጅብ ንክሻ ህይወቷ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ የ4 አመት ህፃን ልጅ በጅብ ንክሻ ህይወቷ ማለፉን የደቡብ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ሳንኩራ ወረዳ ልዩ ስሙ ማዞሪያ በተባለው አካባቢ በመንደሩ የምትኖር የ4 ዓመት ህፃን ልጅ ከእኮዮቿ ጋር እየተጫወተች በነበረበት ወቅት ነው በጅብ ተነክሳ ህይዎቷ ያለፈው፡፡

ጅቡ ህፃኗን በጥርሱ በማንጠልጥል ይዟት ከሮጠ በኋላ በህብረተሰቡ ክትትል ልጅቷን ማስጣል ቢቻልም ጅቡ ባደረሰባት ጉዳት ለህልፈት መዳረጓን ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ጅብ በሰው ላይ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ጠቅሶ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይከሰት ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ እንዳለባቸው  አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.