Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የምገባ ፕሮግራም ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ከክልሉ ዘንድሮ በሁሉም የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመገብ ታቅዶ እየተሰራ የነበረ ሲሆን፥ ዛሬ በሁሉም ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል፡፡

ብቃት ያለው ዜጋ እንዲኖር የሕፃናት እድገት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምገባ ፕሮግራሙ ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.