Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 200 ኩንታል በርበሬ፣ 5 ኩንታል ጨዉ እና 15 ኩንታል ነጭ ሽንኩርት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የካ ክፍ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ200 ኩንታል በላይ የሚሆን በርበሬ፣ 5 ኩንታል ጨዉ እና 15 ኩንታል ነጭ ሽንኩርት መያዙን የከተማዋ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በህገ ወጥ የተከማቹት እነዚህ ምርቶች በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ አካባቢ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ ሳላይሽ እና ጎህ ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው

በኮሚሽኑ የየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ሆን ተብሎ ህዝቡን በማወክ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የተደረገ የስግብግብነት ተግባር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ አመርቂ ስራ ፖሊስ ከህብረተሠቡ እና ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ጋር በመሆን የተሠራ መሆኑን በክፍለ ከተማዉ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አሚር ከሊፍ ገልፀዋል፡፡
ህብረተሠቡ ከእንደዚህ አይነት አላስፈላጊ ድርጊት ሊቆጠብ እንደሚገባ እና እንደቀድሞ ሁሉ ከፖሊስ ጋር መስራት እንደሚገባው ጥሪ መተላለፉን ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.