Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀመረ።

 

የፈተናውን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ ለመስጠት እንዲቻል ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ዩኒቨርስቲ በመግባት ነው ፈተናውን መውሰድ የጀመሩት።

 

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 976 ሺህ 18 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለዘንድሮ ተፈታኞቾ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ” ብለዋል።

 

የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ያሏቸው ተፈታኞቹን፥ “ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት” ብለዋል።

“እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል” ነው ያሉት።

 

“ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነውም” ብለዋል።

 

“የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ” ሲሉም አሳስበዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.