Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ በአማራ ክልል ለውኃ ተቋማት ግንባታ የሚውል የ132 ሚሊየን ብር ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የውኃ ተቋማት ግንባታ የሚውል ከ132 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ያስረከቡት በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ምክትል ዳይሬክተር ኪቲካ ጎዮል÷ ከአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በትብብር እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ ጀኔሬተር፣ የውኃ ፓምፕ እና የሶላር ፓኔልን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፉ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ዳይሬክተሩ÷ በቀጣይም መሠል ድጋፎችን እንሚደረግ አመላክተዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው÷ የውኃ ተቋማት መልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እስካሁን ድረስ ከአጋር አካላት ከ620 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ግብዓቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒሴፍ ያደረገው ድጋፍ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መሆናቸው ፋይዳቸው የጎላ መሆኑንም ዶክተር ማማሩ ገልጸዋል።

እስካሁን በተከናወነ የመልሶ ግንባታ ሥራም ወደ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች የተቋረጠውን የውኃ አገልግሎት መልሰው እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.