የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የቆጠቡ ደንበኞቹን ተሸላሚ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለመጀመሪያ ዙር የቆጠቡ ደንበኞቹን ተሸላሚ አድረገ።
ለውብ ህይወት ይቆጥቡ በሚል ለዘጠኝ ወራት የቆጠቡ ደንበኞቹን ነው ባንኩ በዛሬው እለት ተሸላሚ ያደረገው።
ባንኩ ከ350 ብር በላይ የቆጠቡ የባንኩ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን በመርሐ ግብሩ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት አሸናፊዎች፡-
1ኛ/ እጣ አንድ ባለሁለት መኝታ ቤት ዘመናዊ አፓርታማ፤
2ኛ/ እጣ አንድ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል
3ኛ/ እጣ ሁለት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ
4ኛ እጣ 30 ስማርት ቴሌቪዥኖች
5ኛ/ እጣ 65 ስማርት ስልኮች ተሸላሚ መሆናቸውን በእጣ አወጣጡ ስነስርአት ላይ ለማወቅ ተችሏል።
የባንኩ የሪቴል ባንኪንግ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ደሳለኝ ታደሰ በእጣ አወጣጥ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባንኩ የህብረተሰቡን የቁጣባ ባህል ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ባንኩ የተለያዩ የቁጠባ አገልግሎቶችን መክፈቱን ተናግረዋል።
ባንኩ አሁን ላይ 611 ቅርንጫፎች እንዲሁም 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!