Fana: At a Speed of Life!

የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ገለጸ፡፡
 
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ÷ የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እየሰሩና ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከባድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጥናት የተደገፈ ምቹ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለጹት አቶ ብሩ÷ በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረት እየተሰሩ ከሚገኙ ስራዎች ዋንኛው የኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ማሳደግ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የሚስተዋሉ የማምረቻ ቦታ፣ የፋይናንስና የግብዓት ችግሮችን መፍታትና የዘርፉን የሰውሃይል ልማት ማሰልጠን እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡
 
ይህንን ለማሳካትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠይቅ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት ፡፡
 
በምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የባለፉት ጊዜያት አፈጻጸምና የቀጣይ እቅድ ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መረጃ ያመላክታል ፡፡
 
በመድረኩ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፣ ከሀገር አቀፍና ከክልል የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከብሔራዊ አካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን፣ ከፋሽን ዲዛይን ማህበር፣ ከኢኢግልድ፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከወጣቶችና ሴቶች ፌዴሬሽንና ከሌሎች የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት የመጡ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.