Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 10 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ባንኩ በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለጤና ሚኒስቴር የ10 ሚሊየን ብር ማስረከቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተያያዘ ዜና የተለያዩ ተቋማት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እና የተለያዩ የቅድመ መከላከል ስራዎችን ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስተባባሪነትም በኤግዚቪሽን ማዕከል የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ የማሰባሰብ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር 5 ሺህ ሊትር በረኪና፣ 1 ሺህ 48 የልብስ ሳሙና እንዲሁም 6 ሺህ 452 የገላ ሳሙና ድጋፍ አድርጓል።

ስታር ሳሙና እና ዲተርጀንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ማህበርም 720 ሳሙና በጠቅላላው 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.