ኢትዮጵያና ቱርክ በሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ የበለጠ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የቱርክ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት የመሸከም አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በረራ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
ሁለቱ የአቪዬሽን ባለስልጣናት ከኢስታንቡል -አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ- ኢስታንቡል የመሸከም አቅማቸው ከፍተኛ በሆኑ አውሮፕላኖች በረራ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሃመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት መልካም ግንኙነት ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።