Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ መሪዎች የሕጻናት መቀንጨርን ለማስወገድ ፖለቲካዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ መሪዎች የሕጻናት መቀንጨርን ችግር ለማስወገድ ፖለቲካዊ ድጋፍ እንዲሰጡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጥሪ አቀረቡ፡፡

በኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ መንግስትና የአፍሪካ ልማት ባንክ በሰቆጣ የቃል ኪዳን ስምምነት አተገባባር ዙሪያ ፕሬዚዳንታዊ ምክክር ተካሂዷል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ፥ በትብብር በመንቀሳቀስ በአፍሪካ ያለውን የሕጻናት መቀንጨር ችግር መከላከል እንችላለን ብለዋል።

ባንኩ ለዚህ ተግባር 4 ቢሊየን ዶላር መመደቡንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስድስት ዓመታት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነትን በመተግበር ያስመዘገበው ስኬት ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.