“ሜታ ቡስት “የተሰኘ የኢኮኖሚ አጋዥ ፕሮግራም ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሜታ ከሥራና እና ክህሎት ሚኒስቴር እና ከሰመር ሚዲያ ጋር በመተባበር “ሜታ ቡስት”ን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
“ሜታ ቡስት” የጥቃቅን፥ አነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነስ ባለቤቶች ዲጂታል መሣሪያዎችን ለንግድ ሥራ እድገት እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ እድል የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
ከደንበኞቻቸው ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት ስለሚፈጥሩበት መንገድ የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ እድል ለመስጠት ያለመ የንግድ ስራ ፕሮግራም እንደሆነም ነው የተገለጸው።
በሰመር ሚዲያ እየተተገበረ የሚገኘው ይህ መርሐ ግብር እስካሁን በኢትዮጵያ በነበረው የሙከራ ጊዜ ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ አነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶች የሜታ መተግበሪያዎች የሆኑትን ፌስቡክ፣ኢንስታግራም እና ዋትስአፕን በመጠቀም በበይነ መረብ የንግድ ሥራቸውን ለማሳደግ የሚያስችላቸውን ሥልጠና መስጠቱም ተነግሯል፡፡
በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን እና በምሥራቅ እና አፍሪካ ቀንድ የሜታ የሕዝብ ፖሊሲ ዳይሬክተር ሜርሲ ንዴጓ ተገኝተዋል።
በማህሌት ተ/ ብርሃን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!