አሸባሪው ሕወሓትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ለ3ኛ ዙር የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ እና አሜሪካ በሽብር ቡድኑ ላይ እርምጃ እንድትወስድ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ።
በሰላማዊ ሰልፉ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲሁም ኤርትራውያን ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ “አሜሪካ የሽብር ቡድኑ የጀመረውን ጦርነት በይፋ በማውገዝ እና ለአፍራሽ ድርጊቱ ተጠያቂ ማድረግ አለባት” በማለት ጠይቀዋል።
ሰልፈኞቹ የተለያዪ መፈክሮችንም አሰምተዋል።