Fana: At a Speed of Life!

በወልዲያና ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከ200 በላይ ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወልዲያ ከተማ አስተዳደር እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአሸባሪው ህወሓትን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ200 በላይ ሰርጎ ገቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዳዊት መለሰ እንደገለጹት÷ የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ ለማድረግ በቅንጅት በተሠራው ስራ 123 የጥፋት ቡድኑ ሰርጎገቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገ ነው።

በተመሳሳይ የህወሓት የሽብር ቡድንን ተልዕኮ ተቀብለው ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 ሰርጎቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዋግኽምራብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር አዱኛ ገብሩ እንደገለፁት÷ የዞኑን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ወቅታዊ ሁኔታውን ያገናዘበ ቅንጅታዊ አሠራር ተዘርግቶ እየተሠራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.