Fana: At a Speed of Life!

በጀመርነው አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀመርነው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በጀመርነው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የዱግዳ እና የቦራ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ የተመለከቱት ክንውን እጅግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ዞን ብቻ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን ጠቁመው÷ ግብርናን ማዘመን የላቀ ውጤት ያስገኛል ብለዋል፡፡

በወረዳዎቹ በመኸር እርሻ 31 ሺህ 67 ሄክታር መሬት በክላስተር የለማ ሲሆን፥ ከለማው መሬት 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ክረምት በሀገር አቀፍ ደረጃ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን፥ በዚህም 112 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
 
በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.