በለንደን የግማሽ ማራቶን ሰለሞን ባረጋና ቀነኒሳ በቀለ ሁለተኛና ሦስተኛ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣መስከረም 1 ፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በእንግሊዝ ለንደን በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ቀነኒሳ በቀለ ድል ቀንቷቸዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን የተሳተፈው ሰለሞን ባረጋ 1 ሰዓት ከ39 ሴኮንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ 1 ሰዓት ከ 1 ደቂቃ ከ02 ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የግማሽ ማራቶን ውድድሩን ኡጋንዳዊዉ አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ቀዳሚ በመሆን ማሸነፉን ከለንደን ማራቶን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።