በወሎ ግንባር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አዲስ ዓመትን በወልድያ ስቴዲየም እያከበሩ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ግንባር የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የዘመን መለወጫ በዓልን በወልድያ ስቴዲየም እያከበሩ ነው።
አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ በወሎ ግንባር የተሰለፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ” መነሻችን ኢትዮጵያዊነት መዳረሻችን ድል ነው፤ ለሃገር ክብር በትግል እናብብ” በሚል መሪ ቃል ነው በዓሉን እያከበሩ የሚገኙት፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የአማራ ክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የዘማች ቤተሰቦች ፣የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በለይኩን አለም