Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ104 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ104 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሠዒድ ባበክር እንደገለጹት÷ የክልሉ መንግሥት የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው ለተገኙ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም በአሶሳ፣ መተከልና ካማሺ ዞኖች የሚገኙ እና የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ 104 የሕግ ታራሚዎች የይቅርታው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በይቅርታ ከተለቀቁት መካከል ስምንቱ ሴቶች መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያላክታል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ዜጎች ወደማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ከወንጀል ተቆጥበው በልማት ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፉም የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.