Fana: At a Speed of Life!

“የአገልጋይነት ቀን” በክልሎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ሀገር አቀፍ የአገልጋይነት ቀን “አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል” በሚል  መሪ ቃል  እየተከበረ ነው፡፡

 

ክልሎችም ቀኑን በተለያዩ መርሐ-ግብሮች እያከበሩ ነው፡፡

 

በዚህም በጋምቤላ  ክልል ቀኑን አስመልክቶ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ  በተገኙበት የፅዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

 

በወቅቱም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ÷  ሁሉም ዜጋ የአገልጋይነት ባሕልን በማዳበር ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ እያከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 

በተመሳሳይ በሀረሪ ክልል  የአገልጋይነት ቀንን በማስመልከት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት  የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል፡፡

 

እንዲሁም ለከተማው ህብረተሰብ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

 

ምንጭ፡-ከክልሎቹ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅኅፈት ቤት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.