Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው 992 ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው 992 ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ ያዘጋጀው መግለጫ
እንደሚከተለው ቀርቧል፦

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለ የዝግጅት ሁኔታ

• በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርመራ የተጠናከረ ሲሆን ስድስት መቶ ሺህ ሰማንያ (600,080) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

• በሙቀት መለያ ካለፉት ውስጥ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት (8,985) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

•በሽታውን ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት የመጡ ተጓዞችን በተጨማሪ በኮረና ቫይረስ መያዛቸውን ማረጋገጥ ከተቻለው 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸውን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት (992) ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የሚደረግ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት አንድ ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት (1285) የሚሆኑት ደግሞ ለ 14 ቀን የጤና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ጤንነታቸው በመረጋገጡ የጤና ክትትላቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

የበሽታው ተመሳሳይ ምልክቶች በማሳየታቸው እንዲሁም ከመጀመሪያው ታማሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸውን ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት አንደ መቶ አስራ ሰስት (113) ተጠርጣሪዎች በተለያየ ጊዜ በለይቶ መቆያ ማእከል እንዲቆዩና የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ሰባ አራቱ (74) ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፤ አምስቱ ( 5) የኮሮና ቨይረስ የተገኘባቸው ታማሚዎች ሲሆኑ በለይቶ ማቆያ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ሰላሳ አራቱ (34 ) ተጠርጣሪዎች በለይቶ ማቆያ ሆነው የለቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

• አምስቱ የኮሮኖ ቫይረስ ታማሚዎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
መንግስት ህብረተሰብ የሚሳተፍባቸወ ቦታዎችን እንደ ትምህርት ቤቶች እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ስብሰባዎችን ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እና ለመቆጣጠር በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፤

ህብረተሰባችን በተለይም የበሽታውን ምልክት ያሳዩ ወይም ተጠርጣሪዎች ተብለው በለይቶማቆያ አካባቢ የሚሆኑ ግለሰቦች ምንም እንኳን ውጤታቸው ነጻ መሆናቸው ቢረጋገጥም የማግለል ባህሪዎችን እንዳይከሰቱ ሀብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እና ስለ ኮሮኖ ቫይረስ ወረሽኝ ምንነት ፤ መከkላከያ መንገዶች በጥልቀት ሊረዳው የሚገባ መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

ትኩረት መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

ሕብረተሰቡ ከዚህ በፊት ማንኛውንም በሽታ ለመከላከል ሲጠቀምባቸው የነበረውን የበሽታ መከላከያ መንገዶች ችላ ሳይል እና ሳይደናገጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እያስተላለፍን እነዚህንም መልዕክቶች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንቀንስ፤

● ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ

● እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ

● ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣

● እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣

● ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣

● በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣

● በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣

● መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት ይከላከሉ!

በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሀገራት የሚመጡ ሰዎች ወይም ንክኪ ያላቸው ማንኛወም ግለሰብ አራሱን ለ 14 ቀን በመለየት በበሽታው አለመያዛቸውን ሲያረጋግጡ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እንመክራለን

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.