Fana: At a Speed of Life!

“አዛኝ ቅቤ አንጓች”! – የአሸባሪው ህወሓት ነገር

ሰሞኑን አፈትልኮ የወጣው የህወሓት ምስጢራዊ ሰነድ ስለ ‹‹ፋኖ›› ምን አለ ? የሽብር ቡድኑ አፈ ቀላጤስ ምን ቀባጠረ ?

“የአማራ ተስፋፊ ኃይል ከፋሽስቱ የፌደራል መንግሥት በሚሰጠው ትዕዛዝ መነሻ እና በቆየ የትምክህት ታሪኩ፣ ተስፋፊነቱ …ከወረራው በላይ የትግራይ ተወላጆችን ስም ማጥፋት፣ የተደራጀ ዘረፋ፣ ግድያና ሴቶችን የመድፈር የመሳሰሉ ወንጀሎችን ፈጽሟል” ይላል የወያኔው ሰነድ፡፡

“ተስፋፊውና የትምክህት ኃይሉ ፋኖ የትግራይ ሕዝብ ጠላት መሆኑን ለዓለም አሳይቷል፤ አካሄዱም በትግራይ ሕዝብ ላይ ባለው ጭፍን ጥላቻ ተመሰረተ ነው፤ ከዚህ ቡድን ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም፤ ይልቁንም ከሁኔታው በመነሳት ቡድኑን በጠላትነት እንፈርጀዋለን” ሲል ያትታል ሰነዱ፡፡

“ይህ ፅንፈኛ የአማራ ተስፋፊ ኃይል በትግራይ ላይ ጫፍ የወጣ ጥላቻ አሳይቷል” ያለው የወያኔው ምስጢራዊ ሰነድ፥ “ይሄ ጠባብ እና ተስፋፊ ኃይል በፍፁም የትግራይ አጋር ሊሆን አይችልም “ በማለት ሕዝብን ይኮንናል።

“የዚህ ኃይል አመራሮች በሕዝብ ጉያ ተደብቀው ስለሚገኙ ምቹ ሁኔታ ካገኙ ዳግም ኃይል አግኝተው መነሳታቸው ስለማይቀር በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የተፈጠረውን መቃቃር የትግራይ ሠራዊት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት እንደሚገባ” ያስገነዘበው ይህ ሰነዱ÷ ይህ ኃይል ራሱን “ፋኖ” ብሎ በመጥራቱ የተወሰደበት እርምጃ በርከት ያሉ የአማራ ታጋይ ኃይሎች ከፌዴራል መንግሥት ጎን ተሰልፈው ለመንቀሳቀስ ያላቸውን ወኔ እንዲቀንስ አድርጎታል” ሲል መሠረት ቢስ ሐቲቱን አስነብቧል፡፡

“ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀምም÷ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመሥራት የተፈጠረውን መሻከርና ክፍተት የበለጠ እንዲጠናከር ማድረግ ይገባል” ይላል የቡድኑ ሐተታ፡፡

እዚህ እና እዚያ የሚረግጠው የሽብር ቡድኑ አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ስለ ፋኖ የአዞ እንባ ሲያወርድ እንዲህ አለ፦ “በፋኖ ላይ የህግ ማስከበር ዘመቻ አደርጋለሁ፣ ፋኖ ኢመደበኛ አደረጃጀት ነው፤ ለኢትዮጵያ አንድነት ጠላት ነው ብሎ ከሁለት ወር በፊት ሲንቀሳቀስ የነበረ አመራር አሁን ተመልሶ ድረስልኝ የሚልበት ምክንያት ሰምቶ የሚሄድ ፋኖ ካለ፡-1ኛ ከትግራይ ሠራዊት ጥይት አያመልጥም፤ የሚቀይረው ነገር የለውም።

2ኛ.ወንድማማችነታችን ነው የሚያዋጣን፣ የማንም መጫወቻ መሆን የለብንም” ሲል የጭንቀት ንግግሩን አሰምቷል።

ሰሞኑን አፈትልኮ በወጣዊ ምስጢራዊ የአሸባሪው ህወሓት ሰነድ እና የጌታቸው ረዳ የማታለያ ንግግር “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” ነው። “አዛኝ ቅቤ አንጓች”።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.