የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የምክክር መድረክ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የፍትሕ ቢሮዎች የ2014 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃፀም በተናጠል ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
በሪፖርቱ የተነሱ ጉዳዮችን አፅንኦት ሰጥቶ በመገምገም ቀጣይ የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም የ2014 በጀት ዓመት የግምገማ ሪፖርት፣ የፍትሕ ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድና ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካች ነጥቦች በዝርዝር ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
የቀጣይ ጉባዔ አጀንዳዎችን የማፀደቅ እንዲሁም ቀጣይ የጉባዔ አዘጋጅ ክልል የመምረጥና የበጀት ዓመቱን የአፈፃፀም አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!