Fana: At a Speed of Life!

የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም በነበረበት እንደሚቆይ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነሳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ እንዲቀጥል የተወሰነ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.