Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2014 በጀት ዓመት 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው 2014 በጀት ዓመት 5 ቢሊየን የአሜሪዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
 
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በስሩ የሚገኙ ተቋማትን የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2015 ቀጣይ አቅጣጫዎችን ገምግሟል፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው÷ አየር መንገዱ ባለፈው በጀት ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ቀውስ ተቋቁሞ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
 
ኩባንያው በበጀት ዓመቱ 6 ሚሊየን 900 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ መንገደኞችን ያጓጓዘ ሲሆን÷ 7 ሺህ 700 ቶን የጭነት አገልግሎት መስጠቱም ተመላክቷል፡፡
 
የተገኘው ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸርም 79 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የገለጹት፡፡
 
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ማሞ ምህረቱ ÷ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን እና ሌሎች ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ያስመዘገበው ውጤት የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.