Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

ዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።

የፕሬዜዳንታዊ ምርጫው የድምፅ ቆጠራ ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በውጤቱም ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት በድጋሚ ተመርጠዋል።

በእጩ ተወዳዳሪነት የቀረቡት አቶ መላኩ ፈንታ 27 ድምፅ ሲያገኙ አቶ ቶኪቻ ዓለማየሁ 17 ድምፅ ማግኘታቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.