Fana: At a Speed of Life!

ከአፋር ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

አሸባሪው ህወሓት የጀመረውን ህዝባዊ እልቂት አለም አቀፉ ማሀበረሰብ ሊያወግዝ ይገባል!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል እና በአማራ ክልል በኩል በከፈተው በከባድ መሳሪያ ህዝብን በማሸበር የጀመረውን አረመኔያዊ ህዝባዊ እልቂት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዝ ይገባል።

ቡድኑ ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ ለሶስት ዙር በአፋር ክልል በኩል በከፈተው ጦርነት ንፁሀን ሴቶችን፣ ህፃናት፣ አዛውንቶችን ያለምንም ርህራሄ በጅምላ ጨፍጭፏል፣ ህዝባዊተቋማትን፣ ሀይማኖች ተቋማትን አውድሟል፣ በርካታቁጥር ያላቸው ንፁሀን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል ለስቃይ፣ ለርሃብ፣ ለእንግልት እና ሞት ዳርጓል፡፡

በንፁሀን ዜጎች የጭካኔ አይነቶችን እያፈራረቀ የፈፀመው አሸባሪው ህወሀት ለዘመናት ተጋምዶ የኖረው የአፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን አብሮነት የሚያሰናክለው ባለመሆኑ፣ አሸባሪ ቡድኑን እንደ ቡድን ነጥሎ በማየት፣ የተከበረው የትግራይ ህዝብን ለመታደግ መድረስ የሚገባቸው የሰብአዊ እርዳታ በአፋር በኩል እንዲያልፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለህዝብ እርዳታ እንዲደርስ የአፋር ህዝብና መንግስት ከፌዴራል ተቋማት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች እና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋር ሲሰሩ ቆይተዋል።

በቀጠናው አሸባሪው ህወሀት የከፈተው አስከፊ ጦርነት እንዲቆም መንግስት የሰላም አማራጭ ቢያቀርብም ሰላም የማይቸው አሸባሪው ህወሀት በመንግስት በኩል የቀረቡ የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው በአፋር ክልል በኩል በፈንቲረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ለአራተኛ ር በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በተመሳሳይም በአማራ ክልል በኩል ጦርነት ከፍቶ ህዝባዊ እልቂት በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡

አሸባሪው ህወሀት ከአሁን በፊት ጦርነት በከፈተባቸው ግምባሮች እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በከፈተው ጦርነት ንፁሀን ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የሰው ማዕበልን በጠቀም ጦርነት ከፍቷል። በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ ዞን በያሎ ወረዳ በኩል ከባድ መሳሪያ ወደ ንፁሀን አርብቶ አደሮች በመተኮስ ህፃናትና ሴቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል፣ ከባድ የሆነ ጉዳትም ድርሷል፡፡

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ቡድኑ በአፋር ክልል እና በአማራ በኩል በከፈተው ጦርነት ከዚህ የከፋ ህዝባዊ እልቂትን ለማስከተል እየሰራ በመሆኑ ይህን ፈፅሞ ከሰብአዊነት የራቀ አረኔዊ በጭካኔ የተሞላ ድርጊት በማውገዝ ከሰብአዊነት ጎን ሊቆም ይገባል!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.