ችግሮችን እየነቀልን፤ ችግኞችን እየተከልን አብሮነትን እናስቀጥላለን- ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሚያለያዩንን ችግሮች እየነቀልን፤ ችግኞችን እየተከልን አብሮነትን ማስቀጠል ይገባል” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር 4 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ከማለዳው ጀምሮ እየተካሄደ ነው።
አራተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በመዲናዋ በ11 ክፍለ ከተሞች እና 121 ወረዳዎች ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ፥ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ፣ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ከንቲባ አዳነች በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ መርሐ ግብሩን ሲያስጀምሩ፥ “ዛሬ የክረምቱ ዘመቻ ቢጠናቀቅም አዲስ አበባን አረንጓዴ የማልበስ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል፡፡
“የሚያለያዩንን ችግሮቻችንን እየነቀልን ችግኞችን እየተከልን አብሮነትን ማስቀጠል ይገባል” ነው ያሉት።
በዚህ ዓመት በከተማ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው፥ አፈጻጸሙ የዛሬውን ጨምሮ 15 ነጥብ 3 ሚሊየን እንደሚደርስ አመላክተዋል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!