በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ከነተጠርጣሪው መያዙን የሰመራ ሎጊያ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ዋና አዛዥ ኮማንደር ቢልኢ አህመድ እንደገለጹት÷ ገንዘቡ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ነው በከተማዋ ልዩ ስሙ ደረቅ ወደብ በሚባል ቦታ የተያዘው።
ለፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ ተደብቆ 6 ሚሊየን 738 ሺህ ብር በላይ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ መያዙን ተናግረዋል።
ይህንን ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረው አሽከርካሪ ከነ መኪናው በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ መጠቆማቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!