አምባሳደር ሙክታር የሹመት ደብዳቢያቸውን ለደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር የሹመት ደብዳቢያቸውን ለደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አቀረቡ።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ አምባሳደር ሙክታር ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ የቀድሞውን የነጻነት ታጋይ እና ፕሬዚዳንት ኒልሰን ማንዴላን ጨምሮ ለበርካታ የነጻነት ታጋዮችን ሥልጠና መስጠቷን አምባሳደሩ አስታውሰዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካ የነጻነት ትግል ላበረከተችው አስተዋፅኦ ምስጋና ችረዋል ።
ፕሬዚዳንቱ ከአምባሳደሩ ጋር በመሆን የሁለቱን ሀገሪት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ነው ያረጋገጡት።
በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና በሌሎች የምጣኔ ሀብት ግንኙነት ዘርፍ ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ይሰራልም ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።