Fana: At a Speed of Life!

የቀጣዩ ሳምንት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ተራዘሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በቀጣዩ ሳምንት የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎችን ማራዘሙን አስታወቀ።

ማህበሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ዓለም ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት በሚል የቀጣዩን ሳምንት የአውሮፓ የክለቦች ውድድር ማራዘሙን አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የዛሬ ሳምንት የሚወጣው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍጻሜ እና የጥሎ ማለፍ ድልድልም ተራዝሟል።

በዚህ መሰረት በቀጣዩ ሳምንት ማንቼስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ፣ ጁቬንቱስ ከሊዮን እንዲሁም ባርሴሎና ከናፖሊ ያደርጉት የነበረው ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጓል።

በተጨማሪም የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ የምድብ ጨዋታዎችም አይካሄዱም።

የጁቬንቱሶቹ ዳንኤሌ ሩጋኒ እና ፓብሎ ዲያባላ እንዲሁም የቼልሲው ሃድሰን ኦዶይ እንዲሁም የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የማንቼስተር ሲቲው ተከላካይ በርናንድ ሜንዲ እና ስማቸው ያልተጠቀሰ ሶስት የሌሲስተር ሲቲ ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለዋል።

በሌላ በኩል የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ዛሬ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በቀጣይ የሊጉ ውድድሮች እጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ማህበሩ ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም ከማካሄድ ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ውድድሮችን እስከ ማራዘም የሚደርስ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደሚችል ከእንግሊዝ የወጡ መረጃዎች
ያመላክታሉ።

ቢቢሲ እና ደይሊ ሜይል የመረጃው ምንጮች ናቸው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.