በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የ9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አስረክቧል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ በድጋፍ ርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ድጋፉ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት መሰብሰቡን ጠቁመው÷ በገንዘብ ሲተመንም 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስና አልሚ ምግቦችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የኦሮሚያ ክልል የሴቶችና ሕጻናት ቢሮ አማካሪ ወ/ሮ ታሪኬ ሱባ በበኩላቸው÷ ድጋፉ በክልሉ በባሌ፣ ጉጂ፣ ቦረናና ሐረርጌ ዞኖች በሚገኙ ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ይውላል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!