በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፀሐይ ኃይልን ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል ማሽን ተሰራ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመሠረታዊ ምህንድስና ሳይንስ ምርምርና ፈጠራ ማዕከል የፀሐይ ኃይልን ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል ማሽንና ከወዳደቁ የውሃ ማሸጊያ ፕላሰቲኮች የእግረኛ መንገድ ኮምፖሲት ምንጣፍ ተሰራ፡፡
የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ኪሎሌ ተስፋዬ እንደገለፁት÷ በተመራማሪ ዶክተር አምባቸው ማሩ እና አቶ አበበ ኃይሌ የተሰራው የፀሐይ ኃይልን ወደ ኢነርጂ ኃይል የሚቀይር ሲስተም የተፈጠረው ለምግብ ማብሳያነት የሚውል ማሽን ነው።
ማሽኑ ሁለት ዓይነት የፓራቦላ ስርዓት በመገንባት ቅልጥፍናውን የመለካት ሥራ ተከናውኖ አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል በማዕከሉ የወዳደቁ የውሃ ማሸጊያ ፕላሰቲኮችን ከአካባቢው በመልቀምና በማፅዳት ከተፈጩ በኋላ በማቅለጥ ተፈጥሯዊ ወይንም ሰው-ሰራሽ ቃጫዎችን እና ጂፕሰም በመጨመር የእግረኛ መንገድ ኮምፖሲት ምንጣፍ ተሰርቷል
ይህ ምርምር በዶክተር ሮትች ጌዲዮን ሀሳብ አመንጪነትና ራሳቸው በዳይሬክተሩ አቶ ኪሎሌ ተሰፋዬ አስተባባሪነት አቶ ፍፁም ኢተፋ እና አቶ ልጃለም ኃይሌ ተባባሪነት የተሰራ ሲሆን÷ ከምርምርነት አልፎ ወደ አነስተኛ ምርታመነት የተሸጋገረ ሥራ መሆኑ ተገልጿል።
ሌላው በማዕከሉ እየተሰራ ያለውና ለውጥ የተገኘበት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል ለመምህራንና ለተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል የሚረዱ 69 የድምፅና የምስል ማስተማሪያዎች ቤተ ሙከራ ለአገልግሎት መዋሉን ከኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት 2 የመካኒካል ዎርክሾፕ፣ 2 የኮምፒዩተር እና 1 የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያቤተ-ሙከራዎች በማደራጀትና 8 ቴክኒካል ረዳቶችን በመመደብ የምርምርና ፈጠራ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!