በሰሜን ወሎ ዞን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን በ2014 በጀት ዓመት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ የተሻለ አፈጻጻም ላስመዘገቡ ወረዳዎች፣ ከተሞች፣ ለዞን ሴክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡